Social Accountability Champion

የማሕበራዊ ተጠያቂነት ጀግና 6 – ሁሴን አባኦሊ

ኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት፤ ጅማ ከተማ ቀርሳ ወረዳ ሰርቦ ቀበሌ

ማሕበራዊ ተጠያቂነት የሚተገበርበት የአገልግሎት ዘርፍ፡- ገጠር መንገዶች            

መተዳደሪያ ሥራ፡- እህል ነጋዴ  

የማሕበራዊ ተጠያቂነት ፈጻሚ አጋር – የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የእርዳታና የልማት ማህበር – ኢሉ ውሜን ኤንድ ቺልድረን ኢንተግሬትድ አሶሴሽን

“በጎ ፈቃደኛ ነህ፤ ያለ ክፍያ ነው የምትሰራው ይሉኛል፡፡ ነገር ግን  በማሕበራዊ ተጠያቂነት አማካኝነት እያገኘን ያለው የአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻሎች ለእኔ ከገንዘብ ክፍያ           ይልቅ  ትርጉም አላቸው፡፡”

ሁሴን አባ ኦሊና የአካባቢው ነዋሪዎች በሰርቦ ከተማ መንገዶች ሲሰሩ በቀበሌአቸው ግን ከመንገድ ሥራ ጋር የተያያዘ አንዳች እንቅስቃሴ እንደሌለ ያስተውላሉ፡፡ የተሻሻሉ የገጠር መንዶች እንዲሰሩላቸው የሚያሰሙአቸው አቤቱታዎች ሰሚ አላገኙም፡፡ ምርቶቻቸውን ለመሸጥ ወደ ሰርቦ ከተማ የሚሄዱ አርሶ አደሮች አስፋልት መንገዱን እስከሚያገኙ፤ ጭቃና ድጥ ለመከላከል ሱሪዎቻቸውን ወደ ላይ ሰብስበው በባዶ እግራቸው መጓዝን ይመርጣሉ፡፡ አካባቢውን ከገበያ ጋር የሚያገናኝ መንገድ ባለመኖሩ የእህል ዋጋ ይንራል፡፡ በብዙ ሥፍራዎች የውሀ ማስወገጃ ቦዮች ባለመኖራቸው ከባድ ዝናብ በዘነበ ቁጥር የቀበሌው በርካታ አካባቢዎች ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ሆነዋል፡ ከዚህም የተነሳ በየዓመቱ ከ40-55 የሚደርሱ ቤተሰብ ወቅቱን ጠብቆ በሚከሰት የጎርፍ አደጋ እየተጠቁ ንብረቶቻቸው ይወድሙባቸዋል፡፡ አመቺ መንገድ ባለመኖሩ ብዙ እናቶች የማይደርስላቸውን አምቡላንስ በመጠበቅ ላይ እያሉ ህይወታቸው አልፏል፡፡  

የማሕበራዊ ተጠያቂነት ግንዛቤ በአንድ ሴክተር ላይ ብቻ ተወስኖ መቅረት እንደሌለበት ያመኑት ሁሴንና ሌሎች የቀበሌ ማሕበራዊ ተጠያቂነት ኮሚቴ አባላት በኢሳፕ2 የሽግግር ወቅት ማሕበራዊ ተጠያቂነትን ከትምህርት ዘርፍ ወደ መንገድ ዘርፍ አስፋፉት፡፡ የማሕበራዊ ተጠያቂነት ግንዛቤ መፍጠሪያ ፕሮግራሞቻቸውን 30 ሰዎች በታቀፉባቸው 8 ቡድኖችአካሄዱ፡፡ የፊት ለፊት ውይይትን ተከትሎ በተዘጋጀው የጋራ የድርጊት መርሃ ግብር መሰረት የከተማው አስተዳደር ለመንገድ ግንባታ ከሚያስፈልገው ወጪ ውስጥ 60 በመቶውን እንደሚሸፍንና ቀሪውን ማሕበረሰቡ በፍቃደኝነት እንዲያዋጣ ጥያቄ አቀረበ፡፡ ሁሴን ቃል የተገባውን የማሕበረሰብ መዋጮ በማሰባሰብ የመንገድ ሥራውን ሳያቋርጥ ተከታትለዋል፡፡  

በአካባቢያችን ለሕዝብ መሰረታዊ አገልግሎት ከሚሰጡ ዘርፎች ብዙዎቹ መሻሻል ያስፈልጋቸዋል፡፡ በጎ ጅማሬ ቢሆንም በአንድ የአገልግሎት ዘርፍ ብቻ የሚደረግ የአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል የማህበረሰቡን ፍላጎቶች ሊያሟላ አይችልም፡፡ ለዚያም ነው የማሕበራዊ ተጠያቂነት ሂደትን ወደ ገጠር መንገዶች፤ ወደ ጤናና ሌሎች ዘርፎች ያስፋፋነው፡፡”

እኚህ የማሕበራዊ ተጠያቂነት ኮሚቴ ጀግና ካደረጓቸው ተሳትፎዎች የተነሳ በሰርቦ ቀበሌ ብር 1,282,081.00 ወጪ የተደረገበት 4.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መንገድና የውሀ ማስወገጃ መስመር ተገንብቷል፡፡ የመንገዱ መሰራት በፈጠረው የትራንስፖርት አቅርቦት የአካባቢው አርሶ አደሮች በቀላሉ ምርቶቻቸውን ወደ ገበያ ማድረስና መጓጓዝ በመቻላቸው የምግብና እህል ዋጋ ትርጉም ባለው መልኩ ቅናሽ አሳይቷል፡፡ አሁን የመንገዱ መሰራት አምቡላንሶች በምጥ ላይ ያለች እናት ለምታደርግላቸው ጥሪ ምላሽ መስጠት አስችሏቸዋል፡፡

አቶ ሁሴን ማሕበራዊ ተጠያቂነትን ከዚህም በላይ ለማስፋፋት ዕቅድ አላቸው፡፡ “በሰርቦ ቀበሌ ቢያንስ ለህሙማን ቀላል የሕክምና ምክር የሚሰጡ ባለሙያዎች ያሉት አንድ መድኃኒት ቤት ሊኖር ይገባል፡፡ በቀበሌው የሚንቀሳቀሱ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞችም የተሟላ  አገልግሎት መስጠት በሚያስችላቸው መልኩ አልተዘጋጁም፡፡ ይህን ከቀበሌ ማሕበራዊ ተጠያቂነት ኮሚቴ አባላትና ከጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ጋር እየተነጋገርንበት ነው፡፡” ብለዋል፡፡

Jimma town, Kersa woreda, Serbo kebele 

SA intervention sector: Rural roads     Occupation: Grain vendor    

Implementing SAIP:  Ethiopian Muslim’s Relief and Development Association – Ilu Women and Children Integrated Development Association

“They say as a volunteer you work for free. But the service improvements we achieve through SA mean more                            to me than monetary rewards.”

Hussein Abaoli and his fellow community members often witness road constructions taking place in different parts of Serbo town but not in their kebele.  Their demand for improved rural roads usually fell on deaf ears. To reach an asphalt road, farmers who travel to Serbo town to sell their products, rolled up their trousers and walked barefoot to avoid the muddy and slippery pathway. The price of grain and food increased due to the absence of a road linking the area with the urban market. Lack of drainage facilities in many areas made most part of the kebele vulnerable to flooding during heavy rainfall.  As a result, 40-55 households were affected by frequent flooding each year and properties were damaged. The absence of a convenient road also resulted in many mothers loosing their lives waiting for an ambulance that can never reach them. 

Convinced that the knowledge of SA should not be confined to one sector, Hussein and other members of the KSAC scaled up SA from the education to the roads sector during the Bridging Phase of ESAP2. SA awareness creation programs were conducted in 8 Geres (existing community structures, each comprising 30 people). During the preparation of a Joint Action Plan that followed an interface meeting, the city administration proposed to cover 60% of the expense for the road construction and requested the community to voluntarily cover the rest of the cost.  Hussein mobilized community contributions for the agreed expense and persistently supervised the road construction.

“Many of the basic public service sectors in our area need improvement. Although a good start, improving services in one sector alone cannot satisfy our community’s needs. The improvement should be all inclusive and multiple sectors should be targeted. That’s why we strive to expand the SA process to the rural roads, health and other sectors. 

As a result of the SAC hero’s involvement, a road extending 4.5 kms and a drainage system was constructed in Serbo kebele with a total budget of ETB 1,282,081.00. The accessibility of transportation helped rural farmers to travel and sell their farm products easily and the price of food items and grain reduced dramatically as a result. The availability of the road also helped ambulances respond to the call of  women in labor.

Ato Hussein further plans to scale up SA to the health sector. He said, “There should be at least one pharmacy in Serbo kebele along with health professionals who can give simple medical advice to patients. Health extension workers in the kebele are also not fully equipped to provide good services. I have started discussing this with members of the KSAC and with health extension workers.”