Social Accountability Champion

የማሕበራዊ ተጠያቂነት ጀግና 5 – አሰፋ ቶላ

ኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት፤ ኩዩ ወረዳ ሊባን ኩራ ቀበሌ

ማሕበራዊ ተጠያቂነት የሚተገበርበት የአገልግሎት ዘርፍ፡- ግብርና             

መተዳደሪያ ሥራ፡- አርሶ አደር  

የማሕበራዊ ተጠያቂነት ፈጻሚ አጋርሁንዴ ኦሮሞ ግራስ ሩትስ ዲቨሎፕመንት ኢኒሺኤቲቭ

“መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለማሕበረሰቤ ተደራሽ የማድረግ ሥራን እቀጥልበታለሁ”

“ሰዎችን እንጂ እንስሳትን ወደ ሆስፒታል መውሰድ አይቻልም” ይላሉ አቶ አሰፋ ቶላ በኦሮሚያ ክልል ኩዩ ወረዳ ከሊብና ቁራ ቀበሌ ርቆ ወደሚገኝ የእንስሳት ሀኪም ቤት ለመድረስ የሚያጋጥማቸውን ችግር እያስታወሱ ሲናገሩ፡፡ የቀበሌው አርሶ አደሮች የእንስሳት ህክምና ለማግኘት ወደ ቦንዴ ጊዳቦ፣ ቱሉ ሚልኪ ወይም ኩዩ ከተሞች ለመድረስ 3 ሰዓት መጓዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህን ረዥም ጉዞ በሚያደርጉበት ወቅት በርካታ እንስሳት ክሊኒክ መድረስ ሳይችሉ ቀርተው ይሞታሉ፡፡

በሊብና ቁራ ቀበሌ በማሕበራዊ ተጠያቂነት ሂደት ውስጥ ተነስተው ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ከተደረጉ የግብርና ችግሮች መካከል የእንስሳት ሀኪም ቤት አለመኖር ይገኝበታል፡፡ በአካባቢው የማሕበራዊ ተጠያቂነት ፕሮግራምን የሚተገብረው ሁንዴ የኦሮሞ ግራስ ሩትስ ዲቨሎፕመንት ኢኒሺኤቲቭ የጋራ የድርጊት መርሃ ግብሩ አካል  አድርጎ ለደረጃ ዲ የእንስሳ ክሊኒክ ግንባታ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡ አቶ አሰፋም ይህ ዕቅድ ተግባራዊ ይሆን ዘንድ ንቁ ተሳትፎ አድርገዋል፡፡  በግንባታ ወቅት የአካባቢያቸው ማሕበረሰብ ብር 25,000 የሚገመት ውሀ የማቅረብ፤ የጉልበትና የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲያደርግ የማስተባበር ሥራ ሠርተዋል፡፡ ሁንዴ ለግንባታ ብር 180,000፤ ለመድኃኒት፣ ለሕክምና መሳሪያዎችና ለቢሮ ዕቃዎች ግዢ ብር 100,000 ድጋፍ አድርጓል፡፡ አቶ አሰፋ ባደረጉት ንቁ እንቅስቃሴ ወጪ በሚቆጥብ አሰራር በወረዳው በአርአያነቱ የሚታይና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት የሚሰጥበት የእንስሳት ክሊኒክ ተገንብቷል፡፡

“አሁን ቀንም ሆነ ሌሊት የማይቋረጥ አገልግሎት እናገኛለን፡፡ በበዓል ቀን እንኳ ቢሆን አገልግሎት ስንፈልግ ለኃኪሙ ስልክ መደወል ብቻ ነው የሚጠበቅብን፡፡ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡    እንደ ገና የተወለድኩ ያህል ይሰማኛል፡፡”

የቀበሌ ማሕበራዊ ተጠያቂነት ኮሚቴን በመምራት ረገድ አቶ አሰፋ የግብርና ዘርፉን የጋራ ትግበራ ዕቅድ በአግባቡ ሥራ ላይ እንዲውል፤ የተሻሻሉ ግብአቶች ሳያቋርጡ እንዲቀርቡ፤ የግብርና ማሰልጠኛ ማዕከላት እንዲሻሻሉና የግብርና ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ተገቢውን ክትትል አድርገዋል፡፡ አቶ አሰፋ በቀበሌ የተመደቡ የግብርና ልማት ሠራተኞች ማሕበረሰባቸውን የማገልገል ተነሳሽነትና ቁርጠኝነታቸው እንዲጨምር አድርገዋል፡፡

ማሕበራዊ ተጠያቂነትን በግብርናው ዘርፍ ዘላቂ እንዲሆን ከማስቻል በተጨማሪ አቶ አሰፋ የማሕበራዊ ተጠያቂነት ሂደትን ወደ ጤና፣ ትምህርነት፣ ውሀና የገጠር መንገድ ዘርፎች እንዲስፋፋ ጥረት አድርገዋል፡፡ አቶ አሰፋ በጤና ማዕከል የሚካሄድ ወሊድ እንዲጨምር ከጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ጋር የተንቀሳቀሱ ሲሆን ለከረ ኩራ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ገቢ ለማሰባሰብ የትምህርት ቤቱ ባህር ዛፍ በጨረታ እንዲሸጥ በማድረግ በትምህርት ቤት ኃብት አስተዳደር ውስጥ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት እንዲጎለብት አድርገዋል፡፡

በአቶ አሰፋ አመራር የቀበሌው ማሕበራዊ ተጠያቂነት ኮሚቴ የወረዳው አስተዳደር የመጠጥ ውሀ ለማጎልበት የሚውል በጀት እንዲመድብ ጥያቄ አቅርቧል፡፡ የወረዳው አስተዳደር ካለበት የበጀት እጥረት የተነሳ ጥያቄውን ውድቅ ቢያደርገውም አቶ አሰፋ ጉዳዩን ወደ ዞን በመውሰድ ጥያቄው አዎንታዊ ምላሽ ሊያገኝ ችሏል፡፡  ለማሕበረሰቡ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለወረዳው በማምጣት በ2008 በጀት ዓመት ከወሰርቢ ወንዝ ለሚጠለፍ የመጠጥ ውሀ ማጎልበትና ወደቀበሌው የሚደርስ መስመር ዝርጋታ የሚውል 4 ሚሊዮን ብር በወረዳው እንዲመድብ ተደርጓል፡፡ እያንዳንዳቸው ለ50 አባ ወራ አገልግሎት የሚሰጡ 4 የውሀ ማከፋፈያ ቦኖዎች ግንባታቸው ተጠናቅቆ ለምረቃ ተዘጋጅተዋል፡፡

Oromia regional state, Kuyu woreda, Liban Kura kebele

SA intervention sector: Agriculture 

Occupation: Farmer

Implementing SAIP:  HUNDEE Oromo Grasroots Development Initiatives  

“I will continue working to make basic public services accessible to my community.”

“You can carry people but not animals to the hospital,” says Ato Asefa Tola, recalling the difficulties of reaching a veterinary clinic located far from Liben qura kebele. Farmers of the kebele had to travel for 3 hours to reach a vet clinic in Bonde Gidabo, Tulu milki or kuyu town. Many animals often don’t make it to the clinic and end up dying during the long travel.

Among the agricultural issues prioritized through the SA process in Liban Kura kebele in Kuyu wereda of the Oromia region was the absence of a vet clinic. As part of supporting the JAP implementation, the Social Accountability implementing partner, HUNDEE, allocated fund to be used for D-type Vet Clinic construction. Ato Asefa played an active role in realizing this plan. He mobilized the community to fetch water and support the construction with labor and material contribution estimated at ETB 25,000. HUNDEE contributed ETB 180,000 for the construction and ETB 100,000 for drug, equipment and furniture. With the active engagement of Ato Asefa, a cost effective and high quality vet clinic which is considered as a model for the woreda itself was constructed.

Now, we get uninterrupted services day and night. Even on holidays, we just need to make a phone call to the veterinarian when we need support. I am so happy. I feel like I was born again.”

Leading the KSAC, Ato Asefa closely followed the effective implementation of the agriculture sector JAP that sustained supply of improved inputs, improved FTC services and use of agricultural technologies. He also managed to enhance the motivation and commitment of Development Agents (DAs) in the Kebele to serve the community. Ato Asefa encourages the community to demand for improved select seeds, fertilizers and pesticides and encourages farmers not to use expired agricultural inputs.

In addition to sustaining the SA process in the agriculture sector, he has made efforts to scale up the process to health, education, water and rural road sectors. He worked with health extension workers to advance institutional delivery and introduced Bid Based sale of eucalyptus trees planted in a school to raise fund for Karre Kura Primary School while also promoting the transparency and accountability of school resource management.

With the leadership of Ato Asefa, the Kebele SAC requested the Woreda Administration to allocate budget for potable water development for the Kebele. The Woreda Administration rejected the request on ground of budget scarcity. Ato Asefa took the case to the Zonal level and received a positive response. He came back with a letter addressed to the woreda administration requesting them to respond to the demand of the community. As a result, the woreda allocated a budget of ETB 4 million in 2016 for potable water development and pipe lines have been stretched from Weserbi River to the kebele. 4 water points that serve 50 households each are ready for inauguration.