Social Accountability Champion

የማሕበራዊ ተጠያቂነት ጀግና 4 – አዜብ ቦጋለ 

አዲስ አበባ ከተማ፤ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7

ማሕበራዊ ተጠያቂነት የሚተገበርበት የአገልግሎት ዘርፍ፡- ትምህርት      

መተዳደሪያ ሥራ፡- ምክትል ር/መምህር  

የማሕበራዊ ተጠያቂነት ፈጻሚ አጋር፡ – የጎዳና ተዳዳሪ  ሴት ህጻናት መከላከያ፣ ተሐድሶና ማቋቋሚያ ድርጅትየኢትዮጵያ ሴቶች በጎ አድራጎት ማሕበራት ሕብረት

“አሁን ጥያቄው ያለው ልጆችን ወደ ትምህርት ቤት መላክ ላይ ሳይሆን ጥራት ያለው ትምህርት ማግኘታቸውን ማረጋገጥ ላይ ነው፡፡”  

በአዲስ አበባ ከተማ መሀል በሚገኝ ትምህርት ቤት ውስጥ ተማሪዎች በድንጋይ ላይ ተቀምጠው ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለማሰብ ይከብዳል፡፡ ወ/ሪት አዜብ ቦጋለ በአራዳ ክፍለ ከተማ በብሔረ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃ ትመህርት ቤት ድንጋዮች ዴስኮችን ተክተው ሲያገለግሉ መጀመሪያ እንደተመለከቱ ተመሳሳይ ስሜት ተሰምቷቸው ነበር፡፡ በትምህርት ቤት ውስጥ ያሉ ዴስኮች በርካታ ቁጥር ያላቸውን የምሽት ክፍለ ጊዜ ተማሪዎችን ማስተናገድ አልቻሉም፡፡

ብሔረ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በዋና ከተማ ውስጥ እንደሚገኝ ትምህርት ቤት አገልግሎቶቹን ያሟላ አልነበረም፡፡  የቧንቧ ውሀ መቅጃዎቹ መንግስት ካስቀመጠለት ለ20 ተማሪዎች 1 መቅጃ ደረጃ ርቆ ለ530 ተማሪዎችና መምሕራን አንድ የውሀ መቅጃ ብቻ ነበር የነበረው፡፡ የትምህርት ቤቱ መጫወቻ ሜዳ በአቧራና በወደቀ ሕንጻ ፍርስራሽ የተሞላ ነበር፡፡ ቤተ መጽሐፍቱ የአንድ ክፍል ተማሪዎች ብቻ የማስተናገድ አቅም የነበረው ሲሆን በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ 2 መጸዳጃ ቤቶች ብቻ ነበሩ፡፡ የትምህርት ቤቱ ም/ርዕሰ መምህርት አዜብ ቦጋለ እንደሚያስታውሱት ከሥራ ባልደረቦቿቻቸው ጋር ቢሮ ብቻ ሳይሆን ወንበርም ጭምር ይጋሩ ነበር፡፡ “በቢሮው ውስጥ አንድ ወንበር ብቻ ነበር የነበረው፡፡ ሦስት ምክትል ር/መምህራንና ዋናው ር/መምህር አንዱ ወንበር ላይ ለመቀመጥ ተራ እንጠብቅ ነበር፡፡” 

እነዚህ በማሕበራዊ ተጠያቂነት ሂደት ወስጥ በትምህርት ቤቱ ማሕበረሰብ አማካኝነት ተለይተው ከወጡት 12 የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች መካከል ጥቂቶቹ ነበሩ፡፡ አገልግሎት ተጠቃሚዎችና አገልግሎት ሰጪዎች በነዚህ ክፍተቶች ዙሪያ በፊት ለፊት ውይይት ወቅት መነጋገራቸውን ተከትሎ የጋራ ድርጊት መርሀ ግብር ተዘጋጀ፡፡    

          “አንድ አገልግሎት ሰጪ ምን መደረግ እንዳለበት ከሩቅ ሆኖ አቅጣጫዎችን ከማሳየት ይልቅ ከተጠቃሚዎችጋር ጊዜ ሰጥቶ በማሳለፍ  ማሕበረሰቡ መሰረታዊ አገለግሎቶችን ለማግኘት የሚያደርጉአቸውን ጥረቶችና በምን ሁኔታ ውስጥ እንደሚያልፉ መመልከትና በአግባቡ መረዳት እንዳለበት ማሕበራዊ ተጠያቂነት አስተምሮኛል፡፡ ያን ጊዜ መፍትሄዎችን ለመፈለግ መነሳሳት ይሆንሻል፡፡”

ለወ/ሪት አዜብ ሥራ ላይ የሚውልን ሀብት እንዴት ማሰባሰብ እንደሚቻል ያስተማራቸው ማሕበራዊ ተጠያቂነት በአገልግሎት አሰጣጥ ሕይወታቸው ውስጥ መሰረታዊ ለውጥ እንዳመጣ ይናገራሉ፡፡ የትምህርት ቤቱ በጀት በቂ ባልሆነባቸው ሁኔታዎች አዜብ ፕሮፖዛሎችን ቀርጸው የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ቀርበው በማነጋገር አማራጭ መፍትሄዎች የሚገኝባቸውን መንገዶች አውቀዋል፡፡ በአዜብ አመቻችነት በትምህርት ቤቱ አካባቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከብር 400,000 በሚበልጥ ወጪ የመጫወቻ ሜዳ አሰርቷል፡፡ 3 የመማሪያ ክፍሎች አንድ ላይ ተደርገው ከፍ ያለ ቤተ መጽሐፍት የተዘጋጀ ሲሆን፤ ብር 70,000 በላይ ወጪ የተደረገባቸው  8 መጸዳጃ ቤቶች የተገነቡ ሲሆን የቧንቧ ውሀ መቅጃዎቹ ብዛት ወደ 32 አድጓል፡፡ አዜብ በትምህርት ቤት ውስጥ የማሕበራዊ ተጠያቂነት ክበብ ከማቋቋም ጀምሮ ማሕበራዊ ተጠያቂነትን ከመንግስት ትምህርት ማሻሻያ ፕሮግራም ጋር በማስተሳሰርና ወርሀዊ የማሕበራዊ ተጠያቂነት ሥብሰባዎች እንዲካሄዱ በማድረግ የማሕበራዊ ተጠያቂነት ሂደት እንዲቀጥል አድርገዋል፡፡

ወ/ሪት አዜብ በወረዳው የፋይናንስ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት አማካኝነት የሚዘጋጁትን ዓመታዊ መድረኮች በመጠቀም በማህበራዊ ተጠያቂነት ዙሪያ ያላቸውን ልምድ ለሁሉም ሴክተሮች ያካፈሉ ሲሆን የማሕበረሰብ ውጤት መስጫ ካርድ የተሰኘውንም መሳሪያ አስተዋውቀዋል፡፡ ወ/ሪት አዜብ ወደ ቀበና መዋዕለ ሕጻናትና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፤ እንዲሁም ወደ ቀበና ጤና ጣቢያ የልምድ ልውውጥ ጉብኝቶች አዘጋጅተዋል፡፡ ማሕበራዊ ተጠያቂነትን አስመልክቶ በሚካሄዱ ዝግጅቶ ላይ መገናኛ ብዙሀንንና የወረዳ ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤትን በመጋበዝ በማሕበራዊ ተጠያቂነት አማካኝነት የተገኙ የአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻሎችን በስፋት አስተዋውቀዋል፡፡     

Social Accountability HERO 4 – Azeb Bogale

Addis Ababa City Administration, Arada Sub City, Woreda 7

SA intervention sector: Education   Occupation:

Deputy School Principal

Implementing SAIP:  Organization for Prevention, Rehabilitation and Integration of Female Streeet Children – Union of Ethiopian Women Charitable Association

“The question is no longer about sending children to school but making sure they get quality education.”

It could be difficult for you to imagine students sitting on a stone to attend classes in a school located in the heart of Addis Ababa. Azeb Bogale, went through this same puzzling feeling, when she first witnessed stones replacing desks at Behere Ethiopia Primary School in Arada Sub city. The desks available in the school were not able to accommodate the large number of evening class students. 

Despite being a city school, Behere Ethiopia Primary School had only 1 water tap for its 530 students and teachers, while the government standard puts the ratio of water taps to students as 1:20. The school’s playground was filled with dust and remains of a fallen building, the library was able to accommodate only a classroom of students and there were only 2 toilets. As the school’s Deputy Principal, Azeb recalls sharing an office and even a chair with her fellow colleagues, “There was only one chair in the office and we, three of the deputy principals and the school principal, had to take turns to sit.”

These were some of the 12 service gaps that were identified by the school community as part of the SA process. These were then discussed by service users and service providers at an interface meeting which led to the preparation of a joint action plan.

“Social Accountability has shown me that a service provider should spend time with the community and witness their struggles for basic services to truly understand what they are going through instead of simply giving directions from afar on what should be done. That’s when you will be motivated to find solutions.”

Azeb calls SA a turning point for her work as a service provider, as it has taught her about resource mobilization. In instances where the school’s budget does not suffice, Azeb learned to explore potential solutions by designing proposals and approaching different stakeholders. Through her facilitation work, the Ethiopian Defense Forces, located around the school, constructed a playground worth over ETB 400,000, 3 rooms were merged to form a bigger library, 8 toilets were constructed with over ETB 70,000 and the number of water taps increased to 32.

From establishing an SA club in the school and linking the process with the government’s school improvement program to facilitating monthly SA meetings, Azeb strives to keep the SA process alive. Azeb uses annual platforms organized by the woreda FTA to share her experience on SA to all sectors and introduce them to the Community Score Card tool. She also facilitated experience sharing visits for Kebena Kindergarten and Primary school and Kebena health center. She has so far invited local media and the woreda communication office to SA related events to promote service improvements achieved through SA.