Social Accountability Champion

የማሕበራዊ ተጠያቂነት ጀግና 3 – ታፈሰ አበራ 

ኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት፤ ሰበታ ከተማ ዲማ 05 ቀበሌ

ማሕበራዊ ተጠያቂነት የሚተገበርበት የአገልግሎት ዘርፍ፡- ትምህርት መተዳደሪያ ሥራ፡- አርሶ አደር  

የማሕበራዊ ተጠያቂነት ፈጻሚ አጋር፡-  ቼሻየር ፋውንዴሽን አክሽን ፎር ኢንክሉዥን- የዘላለም ምንጭ ሕጻናትና ሕብረተሰብ ልማት

“በየዓመቱ  በትምህርት ቤት ውስጥ ሲሻሻሉ የምመለከታቸው ነገሮች ከማሕበራዊ ተጠያቂነት ጋር መስራት እንድቀጥል አበረታቶኛል፡፡”

ላለፉት 15 ዓመታት በሰበታ ከተማ ዲማ ጉራንዳ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የወላጅ፣ መምህርና ተማሪ ማሕበር ሰብሳቢ ሆነው ያገለገሉት የ55 ዓመቱ አቶ ታፈሰ አበራ በዚህ ትምህርት ቤት የሚያስተምሩት የራሳቸው ልጅ ባይኖራቸውም የትምህርት ጥራት ጉዳይ አሳስቧቸው የሚናገሩት ከልባቸው ነው፡፡

የማሕበራዊ ተጠያቂነት መተግበር እንደጀመረ በመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቱ ውስጥ ያሉት የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶች በቡድን ውይይት ወቅት ተለይተው ታወቁ፡፡ በማሕበረሰባቸው ውስጥ ተሰሚነት ያላቸው አቶ ታፈሰ በማሕበራዊ ተጠያቂነት ትግበራ ሂደት ወቅት ማሕበረሰቡን በማስተባበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አደረጉ፡፡ በፊት ለፊት ውይይት ወቅት ተማሪዎች በትምህርት ቤታቸው ውስጥ የመጠጥ ውሀ አቅርቦትን፤ መጸዳጃ ቤቶችንና መማሪያ ክፍሎች ጨምሮ  ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እንዲሰጣቸው ጥያቄ አቀረቡ፡፡ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት አገልግት ሰጪዎች፣ ማሕበረሰቡ፣ መምህራን፣  ተማሪዎች፣ በጎ ፈቃደኞች፣ ባለሀብቶችና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተለይተው ከተቀመጡት የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶች ውስጥ ምላሽ ለመስጠት የየድርሻቸውን ወሰዱ፡፡ ለእያንዳንዱ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የጊዜ ሰሌዳ ያስቀመጠ የጋራ የድርጊት መርሀ ግብር ተዘጋጀ፡፡

ይህን ተከትሎ ሁለት የጥበቃና አንድ የዕቃ ግምጃ ቤት ሰራተኞች ተቀጠሩ፤ 6 ተጨማሪ የቧንቧ ውሀ መቅጀዎች ተገነቡ፤ በጎ ፈቃደኞች በለገሱት ብር 5,000 ተጨማሪ መጽሐፍት ተገዙ፤ የትምህር መርጃ መሳሪያዎችና የማጣቀሻ መጽሐፍት ከግብረሰናይ ድርጅቶችና ከሌሎች ተቋማት በድጋፍ ተገኘ፡፡ ማሕበረሰቡ 500 ሜትር የሚሆነውን የትምህርት ቤቱን ቅጥር ግቢ ለማሳጠር ብር 250,000 መዋጮ አደረገ፡፡ ሁሉንም ክፍሎችና ቢሮዎች እንዲሁም ቤተ-መጽሐፍቱ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ተደራሽ ለማድረግ  በመግቢያቸው ላይ መሸጋገሪያዎች ተሰሩ፡፡ የተለየ ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች ጥያቄ ለመመለስ የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶች በስጦታ የተገኙ ሲሆን ለትምህርት ቤቱ ከተመደበው ዓመታዊ በጀት ላይም ግዢ ተፈጽሟል፡፡ ቤተ-መጽሕፍቱም 20 ተጨማሪ መቀመጫዎች እንዲይዝ ተደርጎ ተስፋፍቷል፡፡  

“የትምህርትን ጉዳይ ከተነሳ የግል ጉዳዬ አድርጌ ነው የምወስደው፡፡ ጎበዝ ተማሪ የነበርኩ ቢሆንም በቤተሰብ ላይ ከደረሰ ችግር የተነሳ ትምህርቴን ያቋረጥኩት ከ8ኛ ክፍል ነበር፡፡ ለዚያም ነው ተማሪዎች ከፍ ያለ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ አመቺ ሁኔታዎችን በመፍጠር ሥራ መጠመድ የምፈልገው፡፡”

ላላፉት አራት ዓመታት የሰበታ ከተማ ምክር ቤት አባል በመሆን ያገለገሉት አቶ ታፈሰ ማሕበራዊ ተጠያቂነት እንደ ዲማ ማገኖ፣ ዳሌቲና አብዲ አብዲቢያ የተባሉ ሌሎች ሦስት ትምህርት  ሲስፋፋ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡  ዲማ ማገኖ የጋራ ትግበራ መርሀ-ግብርን ተግባራዊ የማድረግ ደረጃ ላይ ደርሶ ቤተ-መጽሐፍት በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡

አቶ ታፈሰ  በማሕበራዊ ተጠያቂነት ሂደት ውስጥ በተማሪዎች አገልግሎት ዙሪያ ባሉት ክፍተቶች አማካኝነት የሚፈጠሩ ተጽዕኖዎችን በቅርብ ለመከታተል የቻሉበት ትልቅ እድል እንደተፈጠረላቸው ተናግረዋል፡፡ እነዚህን ክፍተቶች በተደጋጋሚ ወደ ምክር ቤት ለውይይት እያቀረቡ በጀት እንዲጸድቅላቸውና ሲተገበሩም ምክር ቤቱም የራሱን የክትትል ሚና እንዲጫወት አድርገዋል፡፡  በዚህ ዓመት በትምህርት ዘርፍ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት፤ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን መማሪያ ክፍሎች ለማስፋፋት፤ እንዲሁም አጥር፣ መጸዳጃ ቤት፣ ቧንቧ ውሀ መቅጃዎች ማሰራትን ጨምሮ ሌሎች ተግባራትን ለማከናወን ከሃምሳ ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ተመድቧል፡፡

 

Social Accountability HERO 3 – Tafesse Abera

Oromia regional state, Sebeta town, Dima (05) kebele

SA intervention sector: Education   Occupation: Farmer

Implementing SAIP:  Cheshire Foundation Action for Inclusion -Yezelalem Minch Children and Community Development 

“Every year, I see something improving in the school – that motivates me to continue working with SA.” 

When 55 year old Ato Tafesse Abera tells you he cares about the quality of education, he truly means it by having served as chairman of the Parent Teacher Students Association (PTSA) at Dima Guranda Primary School in Sebeta town for the past 15 years. This is despite the fact that he no longer has a child that goes to this school. After the introduction of SA, the service gaps of the primary school were identified through Focus Group Discussions. As an influential member of the community, Ato Tafesse played a significant role in community mobilization during the SA process. In an interface meeting, students asked the school administration for standard services with regards to drinking water, toilets and classrooms among others.  Different stakeholders like service providers, the community, teachers, students, volunteers, investors and NGOs took their share of tasks to address the service gaps identified. A Joint Action Plan that includes a timetable for each task was prepared.

As a result, 2 guards and a store keeper were hired for the school, 6 additional faucets were constructed, additional books were purchased for the library through the financial support of a volunteer with a budget of ETB 5,000 and reference books for students were made available with help gained from NGOs and other companies. The community made a contribution of ETB 250,000 to construct a 500m long fence for the school. In order to make all classes and offices accessible for physically challenged students, ramps were constructed in front of the entrance of classes, offices and the library. Special needs teaching aid materials were received in terms of donation and also purchased using the annual school grant to cater to the requests of students with special needs. The library was enlarged to accommodate 20 additional seats.  

“The issue of education is something I consider so personal. Owing to some family problems, I dropped out of school from grade 8, even though I was a brilliant student. That’s why I want to keep on creating an environment where students can reach greater heights.”

Ato Tafesse who has been serving as Sebeta town’s council member for the past 4 years, has contributed in scaling up SA to three other schools – Dima Magno, Daleti and Abdibiya. FGDs have been established in the schools and the community has scored the identified service gaps. Dima Magno has already started implementing a Joint Action Plan with the construction of a library.

Ato Tafesse says through SA, he has had a great opportunity to closely witness the impacts of service gaps on students. He frequently presents these gaps for discussion at the council, influencing budget approval and playing an oversight role on their implementation. This year, more than 50 million birr was allocated for the education sector to construct secondary schools, expand classrooms of elementary schools, build fences, toilets and water taps among others.