Social Accountability Champion

የማሕበራዊ ተጠያቂነት ጀግና 2 – ዘውዴ አስፋው 

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፤ ቂርቆስ ክ/ከማ ወረዳ 4

ማሕበራዊ ተጠያቂነት የሚተገበርበት ዘርፍ፡- ጤና

መተዳደሪያ ሥራ፡- ጡረታ   

የማሕበራዊ ተጠያቂነት ፈጻሚ አጋር፡-  ሕይወት የተቀናጀ የልማት ድርጅት

“ማሕበረሰቤ የተሻለ አገልግሎት ሲያገኝ እንደማየት ልቤን በደስታ የሚሞላው ነገር የለም፡፡”

ሰኞ ሰኔ 29 2007 ዓ.ም ለአቶ ዘውዴ አስፋው እንደ ሌሎቹ ቀናት ተራ ሰኞ ሆኖ አላለፈም፡፡ ዕለቱ የቂርቆስ ጤና ጣቢያ ለ48 ሺህ ነዋሪዎች አገልግሎት ሊሰጥ በሚችልበት ደረጃ ተገንብቶ የተመረቀበት ቀን ነበር፡፡ ጤና ጣቢያው ለ15 ወራት ያህል በሩን ለተጠቃሚው ሕብረተሰብ መክፈት ሲሳነው የአቶ ዘውዴ ደስታ ብዙም ሳይዘልቅ አበቃ፡፡ ይህም የወረዳው ነዋሪ የጤና አገልግሎት ፍለጋ ወደ አጎራባች ወረዳዎች እንዲሄድ አድርጎታል፡፡ ሕይወት የተቀናጀ ልማት ድርጅት የማሕበራዊ ተጠያቂነት ፕሮግራምን በወረዳ 4 በ2005 ዓ.ም ጀመረ፡፡  

ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አረጋውያን፣ ወንዶችና ለችግር ተጋላጭ ሰዎች የተካተቱበት የቡድን ወይይት ከተደረገ በኋላ የጤና ጣቢያው የአፈጻጸም ድክመት እንደ ዋና ችግር ተለይቶ ወጣ፡፡ በፊት ለፊት ውይይት ወቅት ለጤና ጣቢያው ደካማ እንቅስቃሴ ሁነኛ ምክንያት ተደርጎ የሚጠቀሰው የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር በብር 358,000 ቢገዛም ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን በቂ ኃይል እንዳልተገኘ ከወረዳው ካቢኔ ተገለጸ፡፡ በአቶ ዘውዴ የሚመራው የወረዳው ማሕበራዊ ተጠያቂነት ኮሚቴ ይህን መረጃ ይዞ ወደ ኮርፖሬሽኑ ሄደ፤ ጉዳዩንም ወደ አስተዳደር ምክር ቤት ወሰደው፡፡ ኃይል በተቋረጠ ቁጥር ማሕበረሰቡ የሚያጋጥሙትን ችግሮች በዝርዝር አስረዱ፡፡ ከዚህም የተነሳ ከዓመት በላይ የቆየው ችግር በአምስት ቀናት ውስጥ ተፈታ፡፡

“አገልግሎት ሰጪዎችና ማሕበረሰቡ የየድርሻቸውን ኃላፊነቶች በተገቢ ሁኔታ ሲወስዱ የሚገኘውን የተሻለ ውጤት ማሕበራዊ ተጠያቂነት አሳይቶናል፡፡ ለዓመታት መፈታት ያልቻሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶች በሂደት ውስጥ መፍትሄ ሲያገኙ አይተናል፡፡”

  ጤና ጣቢያው የጤና ባለሙያዎችና የህክምና መሳሪያዎች ያልነበሩት ባዶ ህንጻ ነበር፡፡ የቧንቧ ውሃ የቢሮ ዕቃዎችና መድኃኒቶች ያልነበሩት ሲሆን መጸዳጃ ቤቶቹ ለአካል ጉዳተኞች አመቺ አልነበሩም፡፡ በፊት ለፊት ውይይቱ አማካኝነት በተዘጋጀው የጋራ  የድርጊት መርሃ ግብር መሰረት ሠራተኞችን የመቅጠር፤ የሕክምና መሳሪያዎችንና የቢሮ ዕቃዎችን  የመግዛት ኃላፊነት ለጤና ቢሮ ተሰጠው፡፡ ለአካል ጉዳተኞች የሚሆኑ ሁለት መጸዳጃ ቤቶች ሙሉ ወጪአቸው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ተሸፍኖ ተሰሩ፡፡ የግንባታ ተቋራጩ ክፍያ በማዘግየቱ የተነሳ ተቋርጦ የነበረው የመጠጥ ውሀ መስመር ተቋራጩ ለውሀና ፍሳሽ ባለስልጣን ብር 14,000 አንዲከፍል ትዕዛዝ በመሰጠቱ ተቀጠለ፡፡ እነዚህ ውጤቶች የጤና አገልግሎት ፍለጋ እሩቅ የሚሄዱ ሰዎችን ከድካም አሳርፈዋቸዋል፡፡ አሁን ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጤና ጣቢያ ከቀላል ህመሞች ጀምሮ  እስከ ቀዶ ህክምና ድረስ አገልግሎት በማስፋት በሩን ለሕብረተሰቡ ለተጠቃሚው ክፍት አድርጎ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

አቶ ዘውዴም  ማሕበራዊ ተጠያቂነትን ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውስጥ ወደሚገኙ 2 ጤና ጣቢያዎች በወረዳ 3 ጎተራ መሳለጫ ጤና ጣቢያና በወረዳ 5 ፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ ለማስፋፋት ጥረት አድርገዋል፡፡ በማሕበረሰብ ግንዛቤ መስጫ ሥብሰባዎች በመሳተፍና የልምድ ልውውጥ ጉብኝቶችን በማካሄድ ማሕበራዊ ተጠያቂነትን ሊያስፋፉ ችለዋል፡፡ ከዚህ የተነሳ በውሀ መሳቢያ እጦት ለ5 ዓመታት ይቸገር የነበረው የፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ ማሕበራዊ ተጠያቂነትን መተግበር በጀመረ በአንድ ወር ውስጥ የውሀ መሳቢያ መግዛት ችሏል፡፡  

Social Accountability HERO 2 – Zewde Asfaw 

Addis Ababa City Administration, Kirkos Sub City, Woreda 4

SA intervention sector: Health Occupation: retired

Implementing SAIP:  Hiwot Integrated Development Organization

“Nothing fills my heart with joy as serving my community to get better services.”

For Ato Zewde Asfaw, the 13th of July 2015 was not an ordinary Monday. It was a Monday when Kirkos health center was inaugurated with plans to provide services to at least 48,000 people. But Ato Zewde’s excitement was cut short as 15 months passed before the health center showed any signs of opening its doors to the public. This forced the community residing in woreda 4 to travel to neighboring woredas in search of medical services.

Hiwot Integrated Development Organization introduced Social Accountability to woreda 4 in 2013. Focus group discussions comprised of women, youth, elders, men and vulnerable groups, identified the health center’s inactivity as a major problem. In an interface meeting, the woreda cabinet said that although a transformer was purchased with ETB 358,000, there is still no power from the Ethiopian Electric Corporation, hence the reason for the health center’s inactivity. With this information, the woreda SAC chaired by Ato Zewde approached the corporation and tabled their issues to the administration. They explained in detail the problems the community is facing due to the power interruption. As a result, a problem that has persisted for more than a year was addressed in 5 days.

“Social Accountability has showed us how appropriately shared responsibilities among service providers and the community can lead to better results. Through the process, we have seen service gaps that couldn’t be resolved for years, get solutions.”

An empty building, the health center had no medical professionals and equipment, no water points, no office furniture, no drugs and the toilets were inconvenient for people with disabilities (PwDs).  The Joint Action Plan that resulted from the interface meeting gave the responsibility of hiring staff and purchasing medical equipment and office furniture to the Woreda Health Bureau.  2 toilets were constructed especially for PwDs with full expenses covered by Kirkos sub city. Drinking water service that was interrupted because of a delay in payment from the building’s contractor, was resumed after the contractor was instructed to make a payment of ETB 14,000 to the Water and Sewerage Authority. These results were a source of relief for many as they no longer were forced to travel far to get medical services.

From treating minor ailments to performing surgeries, Kirkos health center has more than opened its doors at present – it has started providing standard services.

Ato Zewde worked to scale up SA to 2 health centers in Kirkos sub city – Gotera Masalecha in woreda 3 and Feres meda in woreda 5. He took part in sensitization programs and experience sharing visits to promote the SA process. As a result, Feres meda which struggled with the absence of a water pump for the past 5 years managed to purchase a water pump in one month following the implementation of SA.