Social Accountability Champion

የማሕበራዊ ተጠያቂነት ጀግና 1 – አስናቀ አይችሉህም 

አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፤ ምስራቅ ጎጃም ዞን እናርጅ እናውጋ ወረዳ፤ ደብረ ወርቅ ከተማ ቀበሌ 01

ማሕበራዊ ተጠያቂነት የተተገበረበት ዘርፍ፡- ትምህርት

መተዳደሪያ ሥራ፡- የትምህርት ቤት ር/መምህር

የማሕበራዊ ተጠያቂነት ፈጻሚ አጋር – ምግባረ ሰናይ ሕጻናትና ቤተሰብ መርጃ ድርጅት

“በማሕበራዊ ተጠያቂነት አማካኝነት የአገልግሎት አሰጣጡን ክፍተቶች ለይቶ ማውጣት የመፍትሄውን 50 ከመቶ እንደማግኘት ይወሰዳል፡፡”

አቶ አስናቀ አይችሉህም በ2007 ዓ.ም የደብረወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤትን አዲስ ር/መምህርነትን የተረከቡት ደረጃቸውን ያልጠበቁ የአገልግሎት አሰጣጦችን ከማሻሻል ኃላፊነት ጋር ነበር፡፡ የማሕበራዊ ተጠያቂነት ፕሮግራም በተጀመረበት ወቅት የትምህርት ቤቱ ማሕበረሰብ ስለ አገልግሎት አሰጣጥ ደረጃዎች ግንዛቤ እንዲያገኙ ተደረገ፡፡ በእነዚህ መረጃዎች መሰረት አገልግሎት ተቀባዮች የቡድን ውይይት አዘጋጅተው የደብረ ወርቅ አንደኛ ደረጃ ት/ቤትን የአገልግሎት አሰጣጥ መንግስት ካስቀመጠው ደረጃ አንጻር መመዘን ቻሉ፡፡ ለእያዳንዱ አገልግሎት አሰጣጥ ነጥብ ለመስጠት የተጠቀሙት ከማሕበራዊ ተጠያቂነት መሳሪያዎች አንዱ የሆነውን የማሕበረሰብ ውጤት መስጫ ካርድ ነው፡፡ አቶ አስናቀ እንደሚያስታውሱት ማሕበራዊ ተጠያቂነት 18 የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶችን ለይተው እንዲያወጡ አስችሏቸዋል፡፡

አቶ አስናቀ ስለእነዚህ የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶች ሲናገሩ “በአንድ መማሪያ ክፍል ውስጥ 4 ወይም 5 የተማሪ መቀመጫዎች የነበሩ ሲሆን ብዙ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለመከታተል በድንጋይ ላይ ለመቀመጥ ይገደዱ ነበር፡፡ መማሪያ ክፍሎቹም እጅግ አቧራማ ነበሩ፡፡ የነበረው ቤተ-መጽሐፍት ትንሽ ከመሆኑ የተነሳ የሚያስተናግደው 6 ተማሪዎችን ብቻ ነበር፡፡ በትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ለ1,370 ተማሪዎች አገልግሎት የሚሰጥ አንድ የቧንቧ ውሀ መቅጃ ብቻ ነበር፡፡ የተለየ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች የራሳቸው የሆነ የመማሪያ ክፍልና በሙያው የሰለጠኑ መምህራን  አልነበሯቸውም፤ በክፍል ውስጥ አራት ሆነው በአንድ መቀመጫ ላይ ይቀመጡ ነበር” ይላሉ፡፡

ከአገልግሎት ሰጪዎች ጋር በሚደረገው የፊት ለፊት ውይይት ላይ ተለይተው የታወቁት ችግሮች ሁሉ ለውይይት ቀረቡ፡፡ በውይይቱ ወቅት ማሕበረሰቡና የትምህርት ቤቱ አስተዳደር እነኚህን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል የጋራ የድርጊት መርሃ ግብር አዘጋጁ፡፡ ዕቅዱም በትምህርት ቤቱ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ተለጠፈ፡፡

አቶ አስናቀ የጋራ የድርጊት መርሃ ግብሩ ወደ ሥራ እንዲተረጎም ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡ ከዚህም የተነሳ የተለየ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች የሚያገለግሉ ሁለት መማሪያ ክፍሎች የተሰሩ ሲሆን መምህራንም ተቀጥረውላቸዋል፡፡ የትምህርት ቤቱን ዓመታዊ በጀት በመጠቀም ብር 15,000 የወጣበት የአካል ጉዳተኞች መሸጋገሪያ ተሰርቷል፡፡ 22 መማሪያ ክፍሎች ወለላቸው በሲሚንቶ የተሰራ ሲሆን ከወረዳው አስተዳደር በተመደበ  490 ሺህ ብር 250 መቀመጫዎችና 180 ጠረጴዛዎች ተገዝተዋል፡፡ 8 የቧንቧ ውሀ መቅጃዎች የተተከሉ ሲሆን ለቤተ-መጽሐፉም ሙሉ ዕድሳት ተደርጎለት ለንባብ የሚሆኑ ቁሳቁሶች ተሟልተውለታል፡፡

ጥር 2009 ዓ.ም ላይ በተካሄደው ውድድር በአቶ አስናቀ የሚመራው የደብረ ወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ባደረጋቸው የአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻሎች ምክንያት ከክልሉ ካሉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ አንደኛ በመሆን ዕውቅና አግኝቷል፡፡ አቶ አስናቀ ላደረጉት ጥረት የክልሉ ትምህርት ቢሮ በባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ በሥራ አመራር የማስተርስ ዲግሪ ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችላቸው የነጻ ትምህርት እድል የተሰጣቸው ሲሆን የወረዳው አስተዳደር ደግሞ አንድ ላፕ ቶፕ ኮምፒውተር ሸልሟቸዋል፡፡ 

“እንደ አገልግሎት ሰጪ በማሕበራዊ ተጠያቂነት ሂደት አማካኝነት የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለይቶ ማወቅ መቻሌ ሥራዬን ቀላል አድርጎልኛል፡፡ ለዚያም ሲባል ማሕበራዊ ተጠያቂነትን የትምህርት ቤታችን ባህል አድርገነዋል፡፡”

እኚህ የማበራዊ ተጠያቂነት ጀግና ማሕበራዊ ተጠያቂነትን ወደ ሌሎች ሦስት ዘርፎች ማለትም ወደ ውሀና የአካባቢ ንጽሕና፤ ጤና፤ እንዲሁም ወደ ግብርና እንዲስፋፋ አድርገዋል፡፡ አቶ አስናቀ ከሦስቱ ዘርፎች ኃላፊዎች ጋር ስብሰባ በማድረግ በደብረ ወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የተገኙትን መልካም ተሞክሮዎች አካፍለዋል፡፡ ኢሳፕ2ን በመተግበር ያገኙትን ትምህርት በእናርጅ እናውጋ ወረዳ ለሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች ያካፈሉ ሲሆን በአሁኑ ወቅት 14 ቀበሌዎች ማሕበራዊ ተጠያቂነትን እየተገበሩት ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ቀበሌዎችም ችግሮቻቸውን በመለየት፤ ቅደም ተከተል በማስያዝ፤ የፊት ለፊት ውይይት በማዘጋጅት፤ ከየማሕበረሰቦቻቸው ጋር በመሆን የጋራ ትግበራ ዕቅድ በመንደፍ ወደ እንቅስቃሴ እየገቡ ይገኛሉ፡፡

አቶ አስናቀም የማህበራዊ ተጠያቂነት ሂደቱን በአግባቡ መዝግቦ በመያዝ በአማራ ክልል ለሚገኙ ሁሉም የሙሉ ሳይክል የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፤ እንዲሁም አዲስ አበባ ከተማ ለሚገኘው ኃየሎም ኣርኣያ ትምህርት ቤት አሰራጭተዋል፡፡ አቶ አስናቀ ማህበራዊ ተጠያቂነትን ለማስፋፋት የትምህርት ቤት የማሕበራዊ ተጠያቂነት ክበባትን በመጠቀም ከማሕበራዊ ተጠያቂነት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ድራማዎችን በማቅረብ ጭምር የሕብረተሰቡን ግንዛቤ እንዲጨምር አድርገዋል፡፡ የፕሮግራሙን ዘላቂነት ለማረጋገጥ በደብረወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ የማሕበራዊ ተጠያቂነት ክበብ ቢሮ ተከፍቷል፡፡ የክበቡ አባላት ከትምህርት ቤቱ አስተዳደር መጠነኛ ድጋፍ ብቻ እየተደረገላቸው የማሕበራዊ ተጠያቂነትን ፕሮግራም ያካሂዳሉ፡፡ 

Social Accountability HERO 1 – Asnake Aychiluhim

Amhara regional State, East Gojjam Zone, Enarj Enawega Woreda, Debre Work town Kebele 01

SA intervention sector: Education  

Occupation: School Principal

Implementing SAIP:  Migbare Senay Children and Family Support Organization 

“Identifying service gaps through Social Accountability is accomplishing 50% of the solution.”

Shouldering the responsibility of changing a school with substandard services, Asnake Aychiluhim took leadership of Debrework Primary School, as the new school principal, in 2015. At the start of the Social Accountability program, members of the school community were given information on service standards. Based on this information, service users were able to evaluate Debre work Primary School’s services in comparison with the government’s service standards by conducting focus group discussions. One of the Social Accountability tools, Community Score Card, was used to give scores to each service. Asnake recalls that the SA process resulted in the identification of 18 service gaps.

Speaking about some of these gaps, Asnake said, “There were only about 4 or 5 desks in a classroom which meant that most students had to sit on stones to attend classes. The classrooms were very dusty. The library we had was too small and was able to accommodate only 6 students and there was only one water tap in the school premise for 1,370 students. Students with special needs had to share 1 desk for 4 and they didn’t have their own separate classrooms. The school also had no teachers who were trained on special needs education.”

All of the service gaps identified were tabled for a discussion with service providers in an interface meeting. During the meeting, the community and the school’s administration prepared a Joint Action Plan to address these issues. The JAP was then posted on a board in the school.

Ato Asnake made great efforts to implement the JAP. As a result, 2 separate classrooms were made available for special needs education while teachers were also recruited for this purpose, gateway for students with disabilities was constructed with a cost of ETB 15,000 using the school’s annual budget, 22 classrooms were cemented, 250 chairs and 180 tables were procured with ETB 490,000 allocated by the woreda administration, 8 water taps were constructed and a library has been fully furnished in addition to purchasing reading materials. 

Recognized for the service improvements it is making, Debrework Primary School administered by Asnake stood first from all schools in the region in a competition held in January, 2017. In recognition of his efforts, the regional education bureau gave Asnake a scholarship for Masters Degree in Management at Bahir dar Univeristy while the woreda administration provided him a laptop as an award.

“The identification of service gaps through the SA process has made my job a lot easier as a service provider. That is why Social Accountability has become a culture in our school.”

The SAC hero has made significant contributions in scaling up Social accountability to three more sectors – water and sanitation, health and agriculture. Ato Asnake arranged meetings with the officials of these 3 sectors and shared with them the best practices of Debre work Primary School. He also distributed good lessons and experiences gained from the implementation of ESAP2 to all kebeles in Enarj Enawga woreda and 14 Kebeles are implementing SA at present. These kebeles are now identifying issues, prioritizing them, organizing interface meeting sessions, preparing joint action plans and implementing it together with the community.

Asnake documented and distributed the SA process to all full cycle schools in Amhara region and to General Hailom Araya School in Addis Ababa. To further promote SA, Asnake has created different community mobilization strategies such as staging SA related dramas and theatres using members of the school’s social accountability club.

Ensuring the sustainability of the program, Debrework Primary School has an office for the school’s SA club. Members of the school club are implementing the SA process with minimal support from the school administration.